ይህ በጥቃት ጥበቃ ዙሪያ የተዘጋጀ ባለ አምስት ተከታታይ ክፍል የበይነ-መረብ ሥልጠና ነው፡፡ ተከታታይ ሥልጠናው የፋሚሊ ሄልዝ ፍሮንቲየርስ (ኤፍ.ኤች.ኤፍ) ታሪክን መሠረት በማድረግ ከጥቃት ጥበቃ ጋር የተያያዙ መሠረታዊ ፅንሰ-ሃሳቦችን ያስተዋውቃል። ፋሚሊ ሄልዝ ፍሮንቲየርስ (ኤፍ.ኤች.ኤፍ) ከጥቃት ጥበቃ ጋር በተገናኙ ተጨባጭ ጉዳዮች ዙሪያ የሚሠራ ምናባዊ የሆነ ብሔራዊ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅት ነው።

የእርስዎ ድርሻ ከኤፍ.ኤች.ኤፍ ቡድን አባላት ጋር አብሮ በመሥራት ወሲባዊ ብዝበዛ፣ ጥቃት እና ወሲባዊ ትንኮሳ አዘል ጥቃቶችን የመከላከል ሥራ አዲስ በሚጀመር ፕሮግራም ውስጥ ዋና ጉዳይ ሆኖ እንዲካተት ማስቻል ነው።